· መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ
ውድ አንባቢያን የዚ ፅሁፍ አላማ
ሰዎች የሚያምኑበትን በፅሐፍ ለማጥላላት ወይም ለማንቋሸሽ አይደለም ከዚህ ይልቅ በህርግጥ እነዚህ መፅሐፍት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል
መሆናቸውንና አለመሆናቸውን አንባቢው ራሱ እንዲገነዘብ ማድረግ ነው።
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 1፡28 ኤርምያስ ኢዮስያስን ከግብፅ ንጉስ ጋር እንዳይዋጋ እንደነገረው ይገልፃል
o
ጥያቄ፦
§
ኤርምያስ
በእርግጥ ኢዮስያስን ከግብፅ ጋር እንዳይዋጋ ነግሮታል?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 1፡30 ኢዮስያስ ብላቴኖቹን ተዋግቼ ደክሜአለሁና ከሰልፍ አውጡኝ አላቸው ይላል
o
ጥያቄ
§
ኢዮስያስ
ብላቴኖቹን ከሰልፍ አውጡኝ ያላቸው ስለደከመው ነው ወይስ ስለተወጋ?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
§
ቀስተኞችም
ንጉሡን ኢዮስያስን ወጉት ንጉሡም ብላቴናዎቹን፦ አጥብቄ ቈስያለሁና ከሰልፉ ውስጥ አውጡኝ አላቸው፡፡ 2 ዜና 35፡23
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ1፡52፣57 ኢየሩሳሌምን የፋርስ ንጉስ እንዳጠፋት ይገልፃል
o
ጥያቄ፦
§
ኢየሩሳሌምን
ያጠፉአት ፋርሳውያን ናቸው?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
§
የከለዳውያን
(የባቢሎናውያን) ንጉስ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው (ዕዝራ 38፡18)
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ ከምዕራፍ ሶስት እስከ ምዕራፍ አራት ድረስ ያለው ታሪክ ከወይን፣ከንጉስና ከሴት ማን ያሸንፋል የሚል ክርክር የሰፈነበት ታሪክ የያዘ ሲሆን በመጨረሻ ፅድቅ ታሸንፋለች በሚል ይደመድማል፡፡ ይህ የሆነው ዳርዮስ በነገሰ በሁለተኛው ዘመን በሁለተኛው ወር በሚያዝያ ነው (መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 4፡6)
o
ጥያቄ፦
§
በዚ
ክርክር ላይ ሴት ታሸንፋለች ብሎ የተከራከረው ዘሩባቤል እንደሆነ መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 4፡13 ይናገራል ለመሆኑ በዚህ ወቅት ዘሩባቤል
የነበረው የት ነው በባቢሎን ወይስ በኢየሩሳሌም?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
§
በእየሩሳሌም
እንደነበር መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል ዕዝራ 4፡24-5፡2
§
ዘሩባቤል
ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሰው በፋርሱ ንጉስ ቂርስ በመጀመሪያ አመት ነው ዕዝራ 1፡1፣2፡2
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 4፡44 ንዋየ ቅዱሳቱን ከኢየሩሳሌም የወሰድወ ቂሮስ እንደሆነ ይገልፃል።
o
ጥያቄ፦
§
ንዋየ
ቅዱሳቱን ከኢየሩሳሌም የወሰደው የፋርሱ ንጉስ ቂሮስ ነው ወይስ የባቢሎኑ ንጉስ ናቡከደናፆር?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
§
ንዋየ
ቅዱሳቱን የወሰደው ናቡከረናፆር ሲሆን ቂሮስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አድርጎአል ዕዝራ 1፡7
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ 4፡45 የፋርስ ሰዎች ይሁዳን ባጠፉአት ጊዜ አይሁድ ቤተ በቅደሱን እንዳቃጠሉ የሚገልፅ ዘገባ አለው
o
ጥአቄ፦
§
ይሁዳን
ያጠፉአት የፋርስ ሰዎች ናቸው?
§
ቤተመቅደሱንስ
ያቃጠሉት አይሁዳውያን ናቸው?
o
መፅሐፍ
ቅዱስ ምን ይላል?
§
ስለዚህም
የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን
ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
|
§
የእግዚአብሔርንም
ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የአለቆቹን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን
ወሰደ።
|
§
የእግዚአብሔርንም
ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፥ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ።2 ዜና መዋዕል 36፡17-19
|
- መፅሐፈ ዕዝራ ካልዕ በ 6፡15 ላይ ስልማናሶር የፋርስ ንጉስ እንደሆነ ይገላፃል።
o
ጥያቄ፦
§
ስልማናሶር
የአሶር ንጉስ ነው ወይስ የፋርስ
o
መፅሐፍ
ቅድስ ምን ይላል?
§
መፅሐፍ
ቅዱስ በ1 ነገስት 17፡13፣18፡9 የአሶር ንጉስ እንደሆነ ይገልፃል፡፡
ታዲያ ከላይ ካየናቸው
ነጥቦች አንፃር መፅሐፈ ዕዝራ ካለዕ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ብሎ ለመናገር ይቻላል መልሱን ለናንተ እተዋለሁ። እኔ ግን እግዚአብሔር
ፈፅሞ የማይዋሽ አምላክ እንደሆነ አምናለሁ።
ያላችሁን ጥያቄም ሆነ አስተያየት በ sint2me@gmail.com ላኩልኝ
ያላችሁን ጥያቄም ሆነ አስተያየት በ sint2me@gmail.com ላኩልኝ
No comments:
Post a Comment