መፅሐፈ ዮዲት

መጽሐፈ ዮዲት
መጽሐፈ ዮዲት ከየአዋልድ መጽሐፍት አንዱ ሲሆን አንዳንዶች የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል አድርገው ይመለከቱታል፡፡ይሁን እንጂ መጽሐፉን በደንብ ላነበበው በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት ከተፃፉት ሌሎች የመፅሐፍ ክፍሎች በተለየ በውሸት የተሞላ የፈጠራ ታሪክ እንደሆነ በቀላሉ ሊገነዘብ ይችላል፡፡
እስቲ ጠቅለል ባለ መልኩ የመጽሐፉን ይዘት እንመልከት፡፡
መጽሐፉ ከምዕራፍ 1-3 ድረስ በነነዌ አገር ለፋርስ በነገሰ ናቡከደናፆር ስለተባለ ንጉስ የውጊያ ታሪክ ይነግረናል፡፡(ዮዲት 1፡1)የዚህ መጽሐፍ ውሸት እንግዲህ ከዚህ ይጀምራል አንደኛ ነገር ናቡከደናፆር የባቢሎን እንጂ የፋርስ ንጉስ አለመሆኑ ነው፡፡በባቢሎን የነገሱ ናቡከዳናፆር ተብለው የሚጠሩ ቢያንስ ሶስት ነገስታት የነበሩ ሲሆን የመጀመሪያው ከ1123-1103 ዓ.ዓ የነገሰው ነው፡፡ሁለተኛው ንጉስ ናቡከደናፆር ደግሞ ከ624-582 ዓ.ዓ የነገሰ ሲሆን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጾ የምናገኘው ይህ ንጉስ ነው ፡፡የዬዲት መጽሐፍ ስለ የትኛው ናቡከዳናፆር ነው የሚጠቅሰው?ስለመጀመሪያው ሊሆን አይችልም ምክንያቱም በዚህ ወቅት ናቡከደናፆር አንደኛ በነገሰ በአስራ አምስተኛ አመት ማለትም 1117 ዓ.ዓ በእስራኤል ሳኦል ንጉስ የሆነበት ጊዜ ሲሆን በወቅቱ ሊቀ ካህን የነበረው እንደ ዬዲት መፅሐፍ አባባል ኢዮአቂም የተባለ ሰው ሳይሆን አኪያ ከሱም በመቀጠል ካህን የነበረው አቢሜሌክ ነበር በተጨማሪም በወቅቱ እስራኤላውያን ላይ ጥቃት ይሰነዝሩ የነበሩት ፍልስጤማውያን እንጂ ባቢሎናውያን አልነበሩም (1 ሳሙኤል 14፡3 ፣ 21፡1-6)፡፡ከዚህም በተጨማሪ ዬዲት መፅሐፍ ስለቤተ መቅደሱ መጥፋት ስለሚገልፅና በዚህ ወቅት ደግሞ ቤተ መቅደሱ ገና ያልተገነባ በመሆኑ በዬዲት መፅሐፍ የተገለፀው ናቡከደናፆር ከ 1123-1103 የነገሰው ናቡከደናፆር አንደኛ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ታዲያ የዮዲት መፅሐፍ የሚጠቅሳቸው ታሪኮች ከ624-582 በነገሰው በንጉስ ናቡከደናፆር ሁለተኛ ዘመን ከተፈፀሙ ታሪኮች ጋር ምን ያህል ይስማማል አንዳንድ ታሪኮቹን አንመልከት፡፡
·         በመጀመሪያ የምንመለከተው በዮዲት መፅሐፍ ስለተጠቀሰው ሊቀ ካህን ይሆናል፡፡ ምዕራፍ 4፡6 በወቅቱ ሊቀ ካህን የነበረው ኢዮአቂም እንደነበር ይገልፃል፡፡ለመሆኑ በዚህ ወቅት ማለትም ከ624- 582 ዓ.ዓ ኢዮአቂም የተባለ ሊከ ካህን በኢየሩሳሌም ነበር?
o   በፍፁም!በዚህም ወቅት ቢሆን ሊቀ ካህን ሆኖ ያገለግል የነበረው ሠራያ ሲሆን በኃላ ናቡከደናፆር ገሎታል፡፡2 ነገሥት 25፡18-21፡፡በመሰረቱ ኢዮአቂም የሚባል ሊቀ ካህን በኢየሩሳሌም ፈፅሞ አልነበረም፡፡ታዲያ ዬዲት በፅሐፍ ከየት አመጣው?መልሱን ለናንተ እተወዋለሁ፡፡
·         ሌላው የማነሳው ነጥብ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ስለነበረው መንፈሳዊ ሁኔታ ነው፡፡መፅሐፈ ዮዲት ምዕራፍ 8፡18 የነበረውን መንፈሳዊነት ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-በዘመናችን ጣኦት የሚያመልክ ሰው አልተነሳም፡፡በእርግጥ በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ እስራኤላውያን በጥሩ ሁኔታ ነበሩ?
o   አልነበሩም!ቀድሞ ነገር እግዚአብሔር ለባቢሎናውያን ለምን አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ….. ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተው ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።ኤርምያስ 1፡15፣16፡፡ታዲያ የዮዲት መፅሐፍ በኢየሩሳሌም ጥሩ መንፈሳዊ ሁኔታ ነበር ያለው ከየት አምጥቶ ነው?
·         የዚህ መፅሐፍ ሌላው አስገራሚ ውሸት አምላክ በዮዲት ተጠቅሞ እስራኤልን ነፃ እንዳወጣ የሚገልፀው ታሪክ ነው፡፡በመሰረቱ እስራኤላውያን በባቢሎን እጅ እንዲወድቁ የፈረደባቸው እግዚአብሔር ነው፡፡መፅሐፍ ቅዱስ የሚለውን እንመልከት፡-
o   ከለዳውያንም የንጉሡንና የሕዝቡን ቤቶች በእሳት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።ኤርምያስ 39፡8
o   ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ለሰባ አበታት ወና እንድትሆን ያደረጉ ሲሆን እዝቦቾንም ለሰባ አመታት በባርነት ገዝተዋል፡፡
ታዲያ ምን መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል?የዮዲት መፅሐፍ ተራ ውሸትን የያዘ የፈጠራ ታሪክ ነው ቢባል አትስማሙም?

ያላችሁን ጥያቄም ሆነ አስተያየት በ sint2me@gmail.com ላኩልኝ
  

No comments:

Post a Comment